Thursday, February 18, 2021

ስነ ስርዓት ኣከባብራ ባዓል 46 ዓመት ለካቲት 11 11-2013 02-17-2021 (Source: Tigrai Media House)

 

ኢትዮጵያ ለጦር መሳሪያ መግዣ ተሸጣለች! (Source: Fetsum Gebremicael)

 ኢትዮጵያ ለጦር መሳሪያ መግዣ ተሸጣለች! 

አብይ አሕመድ በትግራይ ላይ ለሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ጦርነት ማስፈፀሚያ የኢትዮጵያን አንጡራ ሐብት ሁሉ በድብቅ እየሸጠ፤ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ላይ እንደሚገኝ፤ ከአንድ የውጭ ተቋም ከተገኘ ዝርዝር ምስጥራዊ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ 

አብይ አሕመድ ስድስት የተራቀቀ ቴክኖሎጂ የጦር ድሮኖችን፤ ይኸውም ሶስት ከቱርክ ሶስት ከቻይና መንግስታት፤ እንዲሁም 20 ራዳር የተጫኑ ዘመናዊ የጦር ታንኮችን ከሩስያ በድብቅ እየገዛ ነው ይላል ይህ ምስጥራዊ መረጃ፡፡   ይህም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ድሮኖችንና እና በትግራይ ጦርነት የወደሙትን ታንኮች ለመተካት ነው፡፡ 

የመከላከያ ሚኒስትር እና የሰሜን እዝ ከፍተኛ የጦር አዛዦች፤ ከኤርትራ የጦር አዛዦች ጋር በመሆን፤ በትግራይ እያካሄዱት ስላለው ጦርነት 'ጥልቅ' ያሉትን ግምገማ አድርገው በደረሱበት ድምዳሜ መሰረት፤ የእነዚህ የአየርና የምድር ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ በአስቸኳይ ካልደረሰ፤ የውጊያው ሚዛን በአደገኛ ሁኔታ ይዛባል ብለው ካሳወቁ በኋላ ነው፡፡  

ከዚህ የጦር አዛዦች ስጋት ጋር በተያያዘ፤ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በማዕከላዊ እና በደቡብ ትግራይ በተካሄዱ ውጊያዎች ከፍተኛ ኪሳራዎች በመክፈላቸው፤ በተለይ ኢሳያስ አፈወርቅና አብይ አሕመድ መቆጣታቸውንና፤ ሙሉ በሙሉ በጦር መሳሪያ ግዢ ላይ ማተኮራቸውን ይኸው መረጃ አመላክቷል፡፡ 

የትግራይ መከላከያ ሰራዊት በሁመራ ድንበር ሰብሮ ከሱዳን ጋር ኮሪደር እንዳያስከፍትና የውጭ እርዳታ እንዳያገኝ፤ መቐለን ጨምሮ ትላልቅ ከተማዎችንና ስትራተጂክ ቦታዎችን እንዳይቆጣጠር፤ ኢሳያስና አብይ ከጦር አዛዦቻቸው ጋር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውንና፤ እነዚህን የድሮን የአየር ሽፋንና ዘመናዊ ታንኮችን በአስቸኳይ ለማስገባት እየተጣደፉ መሆኑን ነው ይኸው መረጃ ያሰመረው፡፡ 

የእነዚህን ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎች ግዢ ለማስፈፀም ነው፤ ኣብይ ኣሕመድ ከዓለም ባንክ የ15 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመጠየቅ ግርማ ብሩንና ኣሕመድ ሸዲን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የላከው ይላል ይኸው መረጃ፡፡ 

ግርማ ብሩ እና አሕመድ ሽዲ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያመሩት፤ የተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሐብት የሽያጭ ሰነዶችና ስምምነቶችን ይዘው ነው፡፡ ይኸውም የዓለም ባንክ ጋር ስለ15 ቢልየን ዶላር የብድር ውልና አከፋፈል ለመወያየትና ከስምምነት ላይ ለመድረስ፤ እንዲሁም ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ተጨማሪ ድጋፍ ለመፈለግ ነው ይላል፡፡  

የዓለም ባንክ የ15 ቢሊዮን ዶላር ብድሩን በአስቸኳይ እንዲሰጣቸውና፤ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሐብት ሽያጭ ከሚገኘው ገንዘብ፤ በፍጥነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕዳቸውን ከፍለው እንደሚያጠናቅቁ፤ ከዓለም ባንክ ሃላፊዎች ጋር ከነበራቸው ቅድመ ውይይት ግንኙነቶች ለማረጋገጥ ተችሏል ይላል ይኸው መረጃ፡፡ 

ግርማ ብሩና አሕመድ ሸዲ ለዓለም ባንክ ለብድር አከፋፈል በማስረጃነት ከሚያቀርቧቸው የንብረት ሽያጭ እጅግ ምስጥራዊ ሰነዶች ውስጥ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮ ቴሌኮምና የኢንዳስትሪያል ፓርኮች ሽያጭ ሰነዶች ይገኙባቸዋል፡፡ 

አብይ አሕመድ እጅግ ምስጥራዊ በሆነ ሽያጭ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ግማሽ ድርሻ፤ በድብቅ ለቱርክ አየር መንገድ ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደርሶ ተዋውሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት የውጭ ጉዳይና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ደመቀ መኮንን እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሸዲ ወደ ቱርክ ተጉዘው፤ ከቱርክ መንግስትና ከቱርክ አየር መንገድ ጋር የሽያጭ ውል ሰነድ ተፈራርመዋል ይላል ይህ መረጃ፡፡ 

አብይ አሕመድ በተመሳሳይ ድብቅ ሽያጭ፤ የኢትዮጵያ ቴሌኮምን ግማሽ ድርሻ ቮዳፎን ለተባለ ግዙፍ የአውሮፓ ካምፓኒ ለመሸጥ፤ እንዲሁም ኢንዳስትሪያል ፓርኮችን ለቻይና መንግስትና ኩባንያዎች ለመሸጥ፤ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ደርሷል ይላል ይኸው መረጃ፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ይላል ይኸው መረጃ፤  ኢሳያስ አፈወርቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትግራይ ውጊያ ለመሳተፍና የኢትዮጵያን ሰራዊት በሁሉም ዓቅሙ ለመደገፍ በገባው ወታደራዊ ስምምነት መሰረት፤ የአንድ ቢልየን ዶላር ክፍያ ስላልተፈፀመ፤  በእነዚህ ንብረቶች ሽያጭ መፋጠን ላይ ኢሳያስ አፈወርቂ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ይገልፃል::

ይህ ሁሉ ሽያጭና ግዢ እየተደረገ ያለው፤ እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጪ በጥቂት ግለሰቦች ነው፡፡ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት፤ ከፍተኛ የአገሪቱ ሐብት በሙሉ እየተቸበቸበ ነው፡፡ የኢትየጵያ ሕዝብም እንዳንቀላፋ ነው፡፡ #ካሳ_ሃይለማርያም

Attack Drones over Tigray (Source: Military and Foreign Affairs Network)