ከሜቴክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኣገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ተይዘው የተከሰሱ ግለሰቦችን ጉዳይ ኣስመልክቶ የተሰራ ማጠቃለያ።
ይህ ማጠቃለያ ከኣያያዛቸው፣ ክስ ኣመሰራረቱ እና እስክ ኣሁን በፍርድ ሂደቱ የሆነውን ነገር ከህግ፣ ከሞራል፣ ከፍትሓዊነት እና ከጤና ኣኳያ የሚያትት ነው።
(ክፍል 1)
ሀ/ ኣያያዛቸውን በተመለከተ
1. መንግስት በፍትህ ተቋማት ይሰሩ በነበሩ ሰራተኞች ያቀረበው ክስ ያለ ፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ ይይዙ ነበር የሚል ነው። ነገር ግን ከሜቴክ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከማረሚያ ቤት የተያዙ ግለሰቦች ኣንዳቸውም በመያዣ ትእዛዝ ኣልተያዙም። በኣንፃሩ ‘ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ’ ተብለው በየተቋሞቻቸው ከተጠሩ በኋላ ስብሰባው ፌዴራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ ነው ተብለው ሲሄዱ ‘ለምርመራ እንደሚፈለጉ’ ተነግሯቸው የታሰሩ ናቸው።
2. የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከሌላ ኣንድ ጀነራል ጓደኛቸው ጋር ቀድሞ የተዘጋጀ ስልጠና ለመስጠት ወደ ዳንሻ በሚሄዱበት ወቅት በትግራይ ክልል ፖሊስ ኣማካኝነት እንዲቆሙ ተደርገው ‘መኪናችሁ የጦር መሳሪያ ይዛለች ተብሎ ተነግሮናል’ ብለው ከፈተሹ በኃላ የመከላከያ ኣባላት መጥተው እንዲሰጥዋቸው የትግራይ ፖሊስ ኣባላትን ሲጠየቁዋቸው ‘እናንተ ይህንን ለማድረግ ስልጣን የላችሁም፣ የመያዣ ትእዛዝ ያለው ካለ መያዣ ትእዛዙን ይዞ ይምጣ’ ከተባሉ በኋላ የፌዴራል ፖሊስ ኣባላት በሄሊኮፕተር የመያዣ ትእዛዝ ይዘው በመምጣት ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል። በመያዣ ትእዛዙ ስማቸው ያልነበረው ሌላኛው ጓደኛቸው ግን ወደ ስራቸው ኣምርተዋል። በመኪናው ሁለቱ ጀነራሎች ከያዙት ሽጉጥ፣ የስልጠና ሰነዶች እና 2000 ብር ውጭ የተገኘ ነገር ኣልነበረም። ጀነራሉ የተያዙበት ቦታ ከሱዳን ድንበር 70 ኪሎ ሜትር የሚርቅ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት እና መንግስት ባሰራጨው ዜና ላይ ከኣገር ሊሸሹ ሲሉ ተያዙ በሚል ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ስራ ተካሂዶባችዋል። በተመሳሳይ የቀድሞ የደህንነት ተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኣቶ ያሬድ ዘሪሁን በዱከም ከተማ ውስጥ በማረፊያቸው የተያዙ ሆነው ሳለ ወደ ኬንያ ለመሄድ በድንበር ተያዙ የሚል ሓሰተኛ ዜና መንግስት ኣሰራጭቶባችዋል።
ለ/ የቀረበባቸውን ክስና ማስረጃን በተመለከተ
1. በጊዜ ቀጠሮ ወቅት
በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ምርመራው ሲያደርግ የነበረው ፖሊስ ሳይሆን ዓቃቤ ህግ ነበር። ይህንን ጉዳይ የሚመሩ እና የሚመረምሩ ዓቃቤ ህጎች እና ፖሊሶች ኣንድም የትግራይ ተወላጅ ወይም ለነበረው ስርዓት ጥሩ ኣመለካከት ያለው ሞያተኛ እንዳይኖራቸው ተብሎ በተሰጠ ኣቅጣጫ መሰረት በወቅቱ የተደመሩ ወይም የድሮ ስርዓት ተጠቂ ናቸው የተባሉ ሞያተኞች የተደራጁበት ነበር። ይህ ኣካሄድ ትክክል ኣይደለም ያሉ በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ይሰሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ይህንን በማለታቸው በደረሰባቸው ጫና ከስራቸው እንዲለቁ ተገደዋል። እንደዛም ሆኖ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ክርክር ከህግ ኣንፃር ሲታይ፡-
1.1 ምርመራ የተጠርጣሪውን ማሳር የግድ ኣስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተጠርጣሪው ከማያዝክ በፊት ማስረጃዎች ተሰብስበው፣ ተጠርጣሪው ወንጀል መፈፀሙን የሚያሳዩ መነሻዎች በኣግባቡ ተይዘው ከፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ በመጠየቅ ሰው የሚያዝበት ሂደት ነው። የኣሁኑ መንግስት ወደ ስልጣን በመጣ በማግስቱ እውቅና የሰጠው እና እተገብረዋለሁ ያለውን ለኢትዮጵያ ህዝብ “…ከዚህ በኋላ ኣጣርተን እንጂ ኣስረን ኣናጣራም…” በማለት ነግሮ ነበር ። ኣባባሉ ትክክለኛ የህግ ኣካሄድ ነው። ነገር ግን በተግባር ኣልተፈፀመም። ምሳሌ 1 በመዝገብ ቁጥር 238040 እነ ጌታቸው ኣሰፋ የተከሰሱት 6ኛ ተከሳሽ ኣቶ ተስፋዬ ኡርጌ እና 26ኛ ተከሳሽ ኣቶ ማርክስ ፀሓዬ ከጉዳዩ ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር ሳይኖር ቦንቡ ከፈነዳበት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዋዜማ ላይ የተከሰተውን ‘በተቋሙ የተለመደ ኣሰራር’ ከቦንቡ ፍንዳታ ጋር በማያያዝ ስማቸው እንዲጠፋበት ተደርጓል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በስልጣን ያለ ኣግባብ መገልገል በሚል በሌላ ጉዳይ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ ኣልተመሰረተባቸውም። ምሳሌ 2 ሁሉም ከሜቴክ፣ ከደህንነት ተቋሙ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከማረሚያ ቤት እና ከቴሌ የተያዙ ሰዎች ለምርመራ በሚል በኣማካኝ ከ4 ወር በላይ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባችዋል።
1.2 ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዳይወጡ በሚል ኣንድ ዓይነት እና በኣንድ ጊዜ የቀረበ ጥቆማን ‘ለጊዜው ብቻ’ በተለያየ መዝገብ በማደራጀት ጉዳዮችን ሰነጣጥቆ በማቅረብ፣ በኣንዱ ዋስትና ሲፈቀድ ‘ሌላ ኣዲስ ጥቆማ መጥቷል’ እየተባለ ዋስትና የማስከልከል ስራ ተሰርቷል። ለምሳሌ በመዝገብ ቁጥር 225258 እና 232121 ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች 6 ጊዜ ዋስትና ፈቅደውላቸው ፖሊስ እና ዓቃቤ ህግ ተጠርጣሪው ኣዲስ ጥቆማ ቀረበባቸው እያሉ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስ ሲመረምረው የነበረውን የቴሌ ታወር (በመዝገብ ቁጥር 240375 በኋላ ላይ ክስ የሆነውን) ጉዳይ ጭምር በማቅረብ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን ዋስትና ለማስከልከል ኣላማ ሲጠቀምበት ነበር።
1.3 በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ተጠርጣሪዎቹ የፈፀሙትን ተግባር በህዝብ ዘንድ ሚዛናዊ እሳቤ እንዳይያዝ ፖሊስ የፈጠራ ምክንያቶችን ሲያቀርብ ነበር። ምሳሌ 1 ከደህንነት ተቋሙ የቀረቡ ተጠርጣሪዎች ጊዜ ቀጠሮ በሚያየው ችሎት ላይ “ተጠርጣሪዎቹ ከሚሰሩበት ክፍል መርዝ የተከማቸበት መጋዘን ተገኝቷል” እየተባለ ሲቀርብ ነበር። በዚህ ጉዳይ ግን መርዝ የተደረገበት ተበዳይ ነበር ወይም ተቋሙ መርዝ ተጠቅሟል የሚል ክስ ኣልቀረበም። በተመሳሳይ ተጠርጣሪዎች ያላደረጉትን ተግባር ኣድርገውታል ተብሎ በጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ደብዳቤ ላይ ተፅፏል፤ የተደረገውን ኣጋንኖ ማቅረብ እና በዜና ማሰራጨት ከምርመራው በላይ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጥበት ይደረግ ነበር። ምሳሌ 2 ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው በሚቀርቡበት ችሎት ላይ በሶማሌ ክልል የተሰራውን የሞባይል ማስፋፊያ ግንባታ ስራን በተመለከተ ተጠርጣሪው ‘ስራው ወንድማቸው ለሚመራው ኮርፓሬሽን ጥቅም ሲሉ በውል ሰጥቷል’ ተብሎ ሲቀርብ ነበር። ነገር ግን በኃላ ላይ ጉዳዩ በመዝገብ ቁጥር 240375 ክስ ሆኖ ከእነ ሰነዱ ሲመጣ ውሉን የፈረሙት የወቅቱ የቴሌ ስራ ኣስፈፃሚ መሆናቸውን፣ ውሉ በሚፈረምበት ጊዜ (በ2001 ዓ.ም) ሜቴክ ያልተቋቋመ እና ከመከላከያ ሚኒስቴር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተደረገ መሆኑን፣ ወንድማቸው ሜጀር ጀነራል ክንፈም የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት በ2002 ዓ.ም መሆኑን ዓቃቤ ህግ በክሱ ገልፆታል። በሰነድም ተረጋግጧል።
2. በመደበኛ የክስ ሂደት ወቅት
2.1 ዓቃቤ ህግ በህግ ወንጀል ሊሆኑ የማይችሉ ተግባራትን የሃገሪቱ ህግና የተቋማቶቹ መመሪያዎችን በሚጥስ መልኩ የወንጀል ድርጊቶች እንደሆኑ ኣድርጎ ክስ ኣቅርቧል። በህግ መሰረት መቅረብ የሚገባው ክስም ህጎች እና ኣሰራሮች ተጣምመው ከህግ ውጭ ኣቅርቧል። ለምሳሌ፡-
2.1.1 በሃገሪቱ የግዢ ህጎች መሰረት [የፌዴራል መንግስት የግዢና ንብረት ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር 649/2001 ኣንቀፅ 3(2)(ለ)] ኣንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ከሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት በሚያደርጉት ግዢ ላይ በኣዋጁ የተቀመጡ የግዢ ዓላማዎች፣ ስርዓቶች እና ሂደቶች ተከትለው እንድሄዱ ኣያስገድዳቸውም። በኣዋጁ ኣንቀፅ 79 ላይ ደግሞ ኣዋጁን የሚቃወም ማናቸውም ደንብ፣ መመሪያ እና ልማዳዊ ኣሰራር ተፈፃሚነት እንደሌለው ያስቀምጧል። ፓርላማው በቀድሞ የግዢ ህግ (ኣዋጅ ቁጥር 430/97) ያልነበረን ተጨማሪ ልዩ ሁኔታ በተራ ፊደል “ለ” በ2001 ዓ.ም ሲደነግግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በእርሳቸው ሲዋዋሉ/ግዢ ሲፈፅሙ/ መደበኛ የግዢ ስርዓቶችን እና ሂደቶች ይከተሉ ቢባል ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን፣ ከኣንድ መስሪያ ቤት ተቀንሶ/በኣንድ መስሪያ ቤት የደረሰ ጉዳት/ ወደ ሌላ መስሪያ ቤት ሲከፈል/ሌላኛው የመንግስት መስሪያ ቤት ሲያተርፍ/ ዞሮ ዞሮ ገንዘቡ ከመንግስት ቀኝ ኪስ ወደ መንግስት ግራ ኪስ የሚሄድ መሆኑን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በየዘርፋቸው በህግ ሲቋቋሙ የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም የማስጠበቅ ተመሳሳይ ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረጉ ነው። የሃገሪቷ ህግ በዚህ መልኩ የሚደነግግ ሆኖ ሳለ በኣቶ ኢሳያስ ዳኘው የተጀመረን የሶማሌ ክልል የሞባይል ማስፋፊያ ግንባታ ቴሌ ከመከላከያ ጋር ውል በማሰሩ በመዝገብ ቁጥር 240375 እነ ኣማረ ኣምሳሉ በሚል 10 ተከሳሾችን ተከሰውበታል። በመዝገብ ቁጥር 229443 ላይም ሜቴክ ከኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርስትና ሎጂስቲክስ ኣገልግሎት ድርጅት የሁለት መርከቦች ግዢ በማከናወኑ መደበኛ የግዢ ስርዓትን ኣለተከተሉም በሚል በ14 ሰዎች ላይ ክስ ሆኖ ቀርቧል።
2.1.2 የፌዴራል መንግስት የግዢና ንብረት ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር 649/2001 ኣንቀፅ 3(2) (ሀ ላይ እንደተደነገገው የደህንነት እና የመከላከያ እቃዎችን በተመለከተ በተለየ መልኩ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት እንደሚከናወን ተቀምጧል። ነገር ግን ዓቃቤ ህግ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተለየ መልኩ እንዲከናወን ያልወሰነ ስለመሆኑ ከተቋሙ ማረጋገጫ ሳያቀርብ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን በመዝገብ ቁጥር 248994 ላይ ወታደራዊ ራዳርን የሚመለከት እንዲሁም በመዝገብ ቁጥር 229497 ላይ በታንክ ላይ የሚገጠም የመድፍ መከላከያ /ERA BOX/ን የሚመለከት ውል በጨረታ መሆን ነበረባቸው ብሎ ክስ ኣቅርቧል።
2.1.3 የሜቴክ ዋና ዳይሬክተሩ በተቋሙ የግዢ መመሪያው በኣንቀፅ 25.1 ላይ ‘…ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ይረዳል ወይም የተለየ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ሲታመን በኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ትዕዛዝ መሠረት ልዩ ግዥ በማዕከል ሊፈፀም ይችላል’ በማለት ተደንግጎ ይገኛል። በሌሎች የግዢ ህጎች እና መመሪያዎችም በተቋሙ የመጨረሻው ኃላፊ ትእዛዝ ግዢ ሊፈፀም እንደሚችል ይደንግጋሉ። ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ስልጣን ተሰጥቶዋቸው እያለ ዓቃቤ ህግ ግን ስልጣን ሳይኖራቸው ግዢ እንዲፈፀም ኣዘዙ በሚል ተደጋግሚ ክስ ኣቅርቧል። ዋና ዳይሬክተሩ ጊዚያዊ ኮሚቴ በማቋቋም ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት ኣቅጣጫ መሰረት ግዢ ፈፅሞ እያለ በግዢ መመሪያው ያለውን ሌሎች የግዢ ዘዴዎች እና ሂደታቸው ኣልተከተሉም በሚል በበርካታ የተቋሙ ሰራተኞች ክስ ቀርቦባችዋል። ለኣብነት ያህል በመዝገብ ቁጥር 229498 (የሆቴሎች ግዢ) ፣ በመዝገብ ቁጥር 231823 (የጥገና ጉዳይ) ፣ በመዝገብ ቁጥር 249410 (የመኪኖች ግዢ) እና በመዝገብ ቁጥር 229443 (የመርከብ ጉዳይ) በተከሳሾች ላይ ኣለ ኣግብብ ክስ ቀርቧል።
2.1.4 ዓቃቤ ህግ በሜቴክ እና የቴሌ ግዢዎች ላይ ‘ግዢው በቦርድ ሳይፀድቅ እንደተገዛ የገለፀ ቢሆንም ይህ ስልጣን ከየት የመነጨ እንደሆነ ኣይናገርም። ሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ ወይም የተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ወይም የሌላ አካል ነው ለማለት በግልፅ የተከሣሾችም ሆነ የቦርድ ሥልጣን ወሰን መታወቅ አለበት። በአዋጅ ቁጥር 25/84 ላይ በምዕራፍ 3 ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አቋምና አመራር የተደነገገ ሲሆን በዚህ ምዕራፍ ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥን ካልሆነ በግዥ መግዛትን በተመለከተ ለቦርድ የተሰጠ ሥልጣን የለም። ይልቁንም በአዋጁ ኣንቀፅ 9(2)(ለ) እና ኣንቀፅ 18 መሠረት ኩባንያዎቹ በስራ ኣስኪያጆቻቸው አማካኝነት መብት ያገኛሉ፤ ግዴታ ይቀበላሉ ሲል ተደንግጓል። ዓቃቤ ህግ ቦርድ በቃለ ጉባኤ ይዞ ስለመፍቀዱ ማስረጃ የለም በሚል በርካታ ክሶች ያቀረበ ቢሆንም መጀመሪያው የቦርዱ ስልጣን ስለመሆኑ ግን የሚጠቅሰው ህግም ሆነ የሚያቀርበው ማስረጃ የለም።
ለኣብነት ያህል በኢምፔርያል ሆቴል ጉዳይ ላይ (229498) የሜቴክ ቦርድ ኣውቆት የተገዛ መሆኑን በወቅቱ የቦርድ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበረው ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ የተባለ የዓቃቤ ህግ ምስክር ኣረጋግጧል። ምስክሩ በችሎት ቀርበው “የሪቬራ ሆቴል ግዢ በኣጀንዳነት ተይዞ ለቦርድ እንዲቀርብ በኣጀንዳ ነጥብነት ተይዞ እንዲቀርብላቸው ሲደረግ ‘ቀደም ብላችሁ የኢምፔርያል ሆቴል ስለገዛችሁ’ ይህንን በኣጀንዳነት ኣንይዝም ብለው የቦርድ ሊቀመንበሩ ኣልተቀበሉትም’’ በማለት መስክሯል። በዚህ ምስክርነት ላይ የኢምፔርያል ግዢ ቀደም ብሎ ሲከናወን ቦርዱ ያወቀው እንደነበር ተረጋግጧል። ነገር ግን ቦርዱን ይመሩ የነበሩ ሰዎች በዚህ ጉዳይም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች በወሰኑት ውሳኔ፣ በሰጡት ኣቅጣጫ ስለተደመሩ ወይም የለውጡ ኃይል ኣካል ስለሆኑ ማንም ኣልጠየቃቸውም።
በተመሳሳይ በኣቶ ኢሳያስ ዳኘው ተጀምሮ ሌሎች 3 ሰዎች የተካተቱበት የዩኒቨርስቲ ኔትዎርክ ግንባታ(EthERNet) እና የሶማሌ ክልል የሞቦይል ማስፋፊያ ውሎች በኢትዮ ቴሌኮም (በቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፓሬሽን) ቦርድ መፅደቅ ሲገባቸው እንዳልፀደቁ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ቢሆንም በመንግስት የልማት ድርጅቶች ኣዋጅ ቁጥር 25/84 ኣንቀፅ 14 መሰረት ‘የረዥም ጊዜ የውጭ ብድሮችን’ ካልሆነ በስተቀር ግዢን በተመለከተ ቦርዱ እንዲያፀድቅ ስልጣን ኣልተሰጠውም።
ግዢ ማከናወን እና ማፅደቅ የማኔጅመንቱ የእለት ተእለት ስራ ሆኖ ሳለ የቦርድ ስራ እንደሆነ ተደርጎ ክስ ቀርቧል። ሃገሪቱ ለቴሌኮም ማስፋፊያ ከZTE 1.5 ቢልዮን ዶላር ብድር የተፈራረመች እና ብድሩ በወቅቱ ሃገሪቱን ይመራ በነበረው ድርጅት እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳይቀር እውቅና ተሰጥቶት ቦርዱ ኣፅድቆታል። ምስክሮቹም ብድሩ ሳይፀድቅ ስራው ሊጀመር እንደማይችል ኣስረድቷል።
ኣስተባባሪ ኮሚቴው EthERNetን እንዲሰራ የወሰነው ከዚህ ገንዘብ ላይ ነው። በተቃራኒው ስለመሆኑ ዓቃቤ ህግ በክሱ ኣልገለፀም፤ ማስረጃም ኣላቀረበም። ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው ከ2003 ዓ.ም በኃላ ይመሩት የነበረው Next Generation Project Office (NGPO) የተባለው የስራ ክፍል ከተፈቀደለት በጀት ውስጥ 1.47 ቢልዮን ዶላሩን ተጠቅሞ ፕሮጀክቶቹ ጨርሷል። ጠቅላላ ፕሮጀክቶቹም ኦዲት እንዲደረጉ ዓለም ኣቀፍ ጨረታ ወጥቶ Trac-Automation በተባለ የካናዳ ኩባንያ ኦዲት ተደርጎ ዋጋውም ሆነ ጥራቱ በኣለም ኣቀፍ ስታንዳርድ መሰረት መሆኑን ኣረጋግጦ ሪፖርት ቀርቦ በቦርዱ ፀድቋል።
ነገር ግን ዓቃቤ ህግ በፕሮጀክቱ ላይ የተሰራው የክዋኔ ኦዲት ሳያቀርብ እና ጉዳዩም በትክክል ሳይረዳው ተከሳሽ በዋስትና እንዲወጣ በግዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ሲፈቀድለት ዋስትና ኣስከልክሎ በእስር ለማቆየት ብቻ ክስ እንዲሆን ኣድርጓል። በክርክር ወቅት ዓቃቤ ህግ ከኢትዮ ቴሌኮም የመጡ ምስክሮችን በማስጠናት ግዢው በቦርድ እንዲፀድቅ በ1997 የወጣው የቴሌ የግዢ መመሪያ በኣንቀፅ 1.1 ያስገድዳል በማለት እንዲመሰክሩ የነገራቸው ቢሆንም በዚህ ኣንቀፅ ላይ በቦርድ እንዲፀድቅ የሚያስገድደው የተቋሙ ቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና ዓመታዊ እቅድ (Annual Plan) እንጂ ግዢን ኣይደለም።
ነገር ግን የመመሪያው ግልፅ ድንጋጌ ዓቃቤ ህግ ኣጣምሞ በማቅረብ ፍትህን ለማዛባት ተጠቅሞበታል። በሶማሌ ክልል የተሰራው የቴሌ ታወር ግንባታም ሆነ ማስፋፊያው በተቋሙ ዓመታዊ እቅድ እና ቢዝነስ ፕላን የተካተተ ኣይደለም የሚል ማረጋገጫ ከቦርዱም ሆነ ከቴሌ የትኛውም ክፍል ኣልቀረበም። በኣንፃሩ በሶሜሌ ክልል የተገነባው የሞባይል ማስፋፊያ በሌሎቹ ክልሎች እንደተሰራው በመላ ሀገሪቱ እንዲሰራ ከታቀው የተካተተ ሆኖ በኣከባቢው ከኣልሸባብ እና ሌሎች ኃይሎች ውግያ የነበረ እና የፀጥታ ችግር በመኖሩ የቴሌ ስራ ኣስፈፃሚ ለጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሽሙ በፃፉት ደብዳቤ መሰረት መከላከያ እንዲሰራው የተደረገ መሆኑን ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።
(ይቀጥላል)

See Less
19 Comments
108 Shares
Like
Comment
Comments
Most Relevant
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.