Friday, August 14, 2020

ከሜቴክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ማረሚያ ቤት ተይዘው የተከሰሱ ግለሰቦች ጉዳይ (Source: Wefri Harinet)

 ከሜቴክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ማረሚያ ቤት ተይዘው የተከሰሱ ግለሰቦች ጉዳይ

(ክፍል II)

2.1.5 ዓቃቤ ህግ የሆቴል እና የመርከብ ግዢዎቹ ሜቴክ ከተቋቋመባቸው ዓላማ እና ተልእኮዎች ውጪ ናቸው በሚል ክስ ቢያቀርብም በሜቴክ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 183/2002 በኣንቀፅ 5 (1) እስከ (8) ላይ ተቋሙ የተቋቋመበትን ዓላማ በዝርዝር ካስቀመጠ በኋላ በንኡስ ኣንቀፅ 9 ላይ “ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን ማካሄድ” እንደሚችል ተቀምጧል። ከንኡስ ኣንቀፅ (1) እስከ (8) የተዘረዘሩ ዓላማዎች ለማሳካት ሰራተኞች እንደሚቀጥር፣ የተለያዩ የኣጋርነት እና የንግድ ስራ ውሎች ከኣለም ኣቀፍ እና ከኣገር ውስጥ ተቋማት እንደሚዋዋል፣ ለወታደራዊ እና ኮሜርሻል ፕሮጀክቶች እንግዶች፣ የቢዝነስ ደንበኞች እንደሚያስተናግድ፣ ለጥናት ስራዎች /ፕሮቶታይፕ/ የሚመች የጥናት ቦታ ሊኖረው እንደሚገባ ለእነዚህ ተግባራትምም ወጪዎች እንደሚያወጣ ግልፅ ነው።

ይህ ዓላማውን ለማሳካት የሚያወጣው ኣይቀሬ የሆነ ወጪ በዘላቂነት ሊቀንስ የሚችል ኣቅጣጫ ተከትሎ ‘ደህንነቱ የተጠበቀ (በተለይ ለወታደራዊ እና ሚስጥራዊ የስራ ጉዳዮች)፣ ሜቴክ በራሱ የሚቆጣጠረው፣ በየሆቴሎቹ እና እንግዳ ማረፊያዎች የሚሰጠውን የተበጣጠሰ እና የተበታተነ ኣገልግሎት በኣንድ ላይ የሚያደርግ፣ ለራሱ ኮሜርሻል እና ወታደራዊ ፕሮጀክቶች ጥናት እና የፕሮቶታይፕ ስራዎች ሊሰራበት የሚችል’ የራሴ ሆቴል/ገስት ሃውስ/ ይኑረኝ ብሎ መግዛቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ ነው ኣያስብልም። ምክንያቱም ዓላማውን ለማሳካት የሚረዳ ሌላ ስራ እንዲሰራ ደንቡ ይፈቅድለታል።

በተመሳሳይ ሜቴክ በኢንጅነሪንግ ጉዳዮች ጥናት ማድረግ፣ ማሻሻል፣ ማዳቀል፣ መቅዳት፣ ማምረት፣ መጠገን ወዘተ ኣከናውኖ ለኣገር ኣበርክቶ እንዲያደርግ መቋቋሙን ማቋቋሚያ ደንቡ ያስረዳል። በተግባርም በተሽከርካሪ፣ ባቡር እና ኣውሮፕላን ጥገና፣ ማምረትና መግጠም የኢንጅነሪንግ ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ ይገኝ ነበር። በመርከብ ኢንጅነሪንግ ዘርፍም በጥገናው፣ በማምረቱም ይሁን በማሻሻል ዘርፉ ልሰማራ ማለቱ ከተልእኮው ውጪ ነው ኣያስብልም። የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ኣገልግሎት ድርጅትም የጥገና ውል ለማግኘት ከሜቴክ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈርሞ ነበር። በየጊዜውም የኢትዮጵያ መርከቦች በኣገር ውስጥ ኣቅም ለመጠገን ተብሎ እቅድ ሲያዝ ቆይቷል። ከዚህ ኣንፃር በዚህ ዓላማ መነሻነት ለኢንጅነሪንግ ዘርፉ መጎልበት ይረዳሉ ተብለው መገዛታቸው ከተልእኮ ውጪ ሊባል ኣይችልም። መርከቦቹ የሚፈርሱበትን ቦታ እስኪከራይ በጊዜያዊነት በትራንስፖርት ዘርፉ ተጠግነው ይሰማሩ በሚል ውስኔ መስጠትም ሆነ መሰማራትም ከኣንቀፅ 5(9) ኣንፃር ከተልእኮ ውጪ ነው ሊባል ኣይችልም።

2.1.6 ሜቴክ በኮርፖሬሽኑ ማቋቋሚያ ደንብ 183/2003 በአንቀፅ 5(4) ላይ “…Through creating Partnership/በኣጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ/…” በማለት በአጋርነት መርህ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን፣ በግዢ መመሪያው ከኣንቀፅ 25.2 – 25.9 ባሉት ድንጋጌዎች ደግሞ ሳብ ኮንትራክተሮችን በማወዳደር ኣደራጅቶ ከእነሱ ጋር የማእቀፍ ወይም የአጋርነት ስምምነት (Collective/Umbrella) Agreement) በመፈራረም ከስሩ ያሉ ኢንዱስትሪዎች እና የስራ ክፍሎች በቀጥታ የማእቀፍ ስምምነቱ ከፈረመው ኣጋር ጋር ውል እንዲያስሩ ይፈቅድላችዋል። አጋሮቹ የሚደራጁበት እና የማእቀፍ ስምምነት የሚፈርሙበት ኣሰራር ደግሞ በመመሪያ METEC/OP/CO/01 በተቋሙ ቦርድ ፀድቆ ተግባራዊ ሆኗል። በዚህ ኣግባብ የተደረጉ ውሎችን በጨረታ መደረግ ነበረባቸው በማለት ክስ ሆኗል።

የኣጋርነት መመሪያውም መንግስት ባሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም ላይ የኣጋርነት መመሪያው የተቋሞቹ ኣመራሮች እርስ በእርስ እና የሆነ ቡድን ለመጥቀም ሲሉ የፈጠሩት ነው በማለት ኣቅርበውታል። መመሪያው ግን ለቡድን ወይም ለግለሰብ ሳይሆን በመመሪያው የተመለከተውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚገለገልበት ነው። መመሪያው ሳይሻር እና ሂደቱን ጠብቆ በተቋሙ ቦርድ የፀደቀ ሆኖ ሳለ ይህንን ወደ ጎን ተትቶ ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች እንዲከተሉት የሚያስገድደውን ህግ ኣልተከተላችሁም በሚል ክሶች ቀርበዋል።

ለኣብነት ያህል በመዝገብ ቁጥር 249579 (የሕዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበት ቦታ ደን ምንጣሮ)፣ በመዝገብ ቁጥር 245570 [የሕዳሴ ግድብ የውሃ መፍሰሻ (Bottom Outlet) የብየዳና የእርማት ስራ (Weding and Welding Repair)]፣ በመዝገብ ቁጥር 229497 (በታንክ ላይ የሚገጠም የመድፍ መከላከያ /ERA BOX/)፣ በመዝገብ ቁጥር 231823 (የህንፃ ጥገና)፣ በመዝገብ ቁጥር 229722 (የትምህርት ጉዳይ)፣ በመዝገብ ቁጥር 229396 (የትራክተር ኣካላት ግዢ ጉዳይ)፣ በመዝገብ ቁጥር 231800 (የጣና በለስ እና ኦሞ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ቁጥር 1 የኃይል ማመንጫ ተርባይን ተከላ)፣ በመዝገብ ቁጥር 232110 (የከረንት ትራንስፎርመር ኣቅርቦት ውል) ላይ የግዢ ውሎቹ የተፈረሙት ከኣገር ውስጥ እና ከውጭ ኣገር ኣጋር ማሕበራት ናቸው።

ስራውን በውል የወሰዱት ግለሰቦች እና ማሕበራት በመመሪያው መሰረት በኣጋርነት የተደራጁ መሆኑን በዓቃቤ ህግ የሰነድ እና የሰው ምስክሮችም ተገልጧል። ነገር ግን ውሉ የመመሪያው ኣንቀፅ 25.9 በሚፃረር መልኩ በጨረታ መደረግ ነበረበት የሚል ክስ ቀርቧል። ግዢ በጨረታ ብቻ መደረግ ነበረበት የሚል ህግና መመሪያ ቢኖር ኖሮ በማእቀፍ ስምምነት ቀጥታ ግዢ ማድረግ ይቻላል የሚል ሌላ ድንጋጌ ኣያስፈልግም ነበር።

ኣንዳንዶቹ ግዢዎች ደግሞ በጭራሽ በጨረታ ሊካሄዱ የማይችሉ ናቸው። ለኣብነት ያህል በሕዳሴው ግድብ ላይ ድሮም ሆነ ኣሁን ጨረታ ወጥቶ ኣያውቅም፤ ጨረታ ማውጣቱ ከፍተኛ የጊዜ መጓተት በመፍጠር ኣገር ለኪሳራ የሚዳርግ እና በተቻለ ፍጥነት ሊገኝ የሚችለውን ኣገራዊ ጥቅም ስለሚያሳጣ። ሆኖም ግን የሕዳሴው ግድብ የምንጣሮ ስራም በጨረታ መደረግ ነበረበት የሚል ክስ ቀርቧል።

ሌላው ኣብነት የትራክተር ኣካላት ግዢ ነው። ዓቃቤ ህግ ውሎቹ ትራክተር ለመግዛት እንደተደረጉ የገለፀ ቢሆንም ትራክተር ለመግዛት ግን ውል ኣልተፈፀመም። ለምሳሌ IMR ከተባለ የሰርቢያ ኩባንያ ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም የተፈረሙ ውሎች ከመግቢያቸው ጀምሮ ሲታዩ ‘ፈቃድ የመከራየት (Under License Agreement)’፣ በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ ምርቶች በሁለቱም ኩባንያዎች የንግድ ምልክት ማለትም ‘RAKOVICA’ እና ‘METEC’ በሚል ጣምራ ስም እንዲሰጣቸው፣ ኩባንያው የትራክተር ኣካላት እና መለዋወጫቸውን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች የተወሰኑት በSKD (Semi Knock Dawn) የሚበዙት ደግሞ በCKD (Complete Knock Dawn) መልኩ ለተከታታይ 7 ዓመታት ሊያቀርብ (በእድሳት ለተጨማሪ 3 ዓመት ሊራዘም መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ)፣ የውሉ ስያሜም የንግድ እና የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት (Contract of Business and Technical Cooperation, Cooperation based on Mutual Consideration and Confidence) የሚል ነው። ይህም ፈቃድ ኣከራዩ እና ጥሬ እቃ ኣቅራቢው IMR ሙሉ የምርትና ኣመራረት ዶክመንቶች፣ ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ትራክተሩ ከመጀመሪያው የኣመራረት ሂደት እስከ መጨረሻው የኣገጣጠም ሂደቱና ፍሰቱ የሚያሳዩ መገጣጠሚያ ቻናል በኣዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪ/የቀድሞ ናዝሬት ትራክተር መገጣጣሚያ ፋብሪካ/ በመስራት የሚከናወን መሆኑን የውሉ ኣንቀፅ 6 እና 7 ያሳያሉ።

በሌሎች የግዢ ውሎችም በተመሳሳይ የትራክተር ኣካላት በSKD (Semi Knock Dawn) እና በCKD (Complete Knock Dawn) መልኩ እንዲቀርቡ ተደርገው የትራክተሮቹ ኣመራረት ከ ‘ሀ’ እስከ ‘ፐ’ በኣገር ውስጥ የሚገጣጠሙበት እና መጨረሻ ላይም በኣገር ውስጥ የራስህ የሆነ ትራክተር በማበልፀግ የሚመረትበት ሂደት የሚያፋጥኑ ናቸው እንጂ ኣንድ ሙሉ ትራክተር ከውጭ ተገዝቶ ለገበያ የሚቀርብበት ሂደት ኣይደለም። ይህ ሂደት ዓቃቤ ህግ በክሱ ላይ ‘በግልፅ ጨረታ መከናወን እየተቻለ እና እየተገባ’ በሚል የገለፀው ቢሆንም ለክስ ዓላማ ካልሆነ በስተቀር ይህ በነባራዊው ዓለም የሚቻል ኣይደለም። የቴክኖሎጂ ውጤትን የሆነን ለምሳሌ ትራክተር በጨረታ ሊገዛ ይችላል። ነገር ግን ትራክተር የሚመረትበት ሂደት/The whole Process and Formula) በጨረታ የሚሸጥልክ ኣንድም ድርጅት በየትም ዓለም ኣይገኝም። መንግስትም ይህንን ስለኣወቀ ሃገሪቱ የቴክኖሎጂ ችግሯን እንዴት መቋቋም እንዳለባት፣ ቴክኖሎጂ እንዴት ከኣደጉ ኣገሮች ማሻገር እና በኣገር ውስጥ ማበልፀግ እንደሚቻል ከኣደጉ ኣገሮች ተሞክሮ በመውሰድ፣ የራሱ ጥናት በማድረግ እና ስትራተጂ ነድፎ፤ የዚህ ስትራተጂ ነፀብራቅም በሜቴክ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 183/2002 በኣንቀፅ 4 ላይ “…Through creating Partnership/በኣጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ/…” በሚል ተገልፆ ይገኛል። ፖሊሲና ስትራተጂዎች ህግ በማውጣት የሚቋጩ ናቸው። ከዚህ ህግ መውጣት ጀርባ የነበረውን ፖሊሲ፣ ዝርዝር ስትራተጂ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ዝርዝር ጥናት፣ በጥናቱ ላይ የተደረገ ውይይት እና ውሳኔ በተለይ ቴክኖሎጂ ማልማት ጨረታ በማውጣት የሚሳካ ነው ወይስ ኣይደለም? የሚለውን በግልፅ የሚመልስ ሰነድ በመንግስት እጅ ይገኛል፤ በተለያየ ጊዜም ለመንግስት ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ዓቃቤ ህግ በጨረታ መግዛት እየተቻለ እና እየተገባ በሚል በክሱ የገለፀ ቢሆንም እንዴት እንደሚቻል እና እንደሚገባ የሚሳይ ማስረጃ ኣላቀረበም፤ ሊያቀርብም ኣይችልም። ለዚህ ኣንዱ ማሳያው ኢንዱስትሪው ወደ ሜቴክ ከመሸጋገሩ በፊት ከቤላሩስ/የቀድሞ የሶቬየት ሕብረት መንግስት ኣካል የነበረችው/ የትራክተር ኣካላት እያስመጣ ሲገጣጥም የነበረው በ1977 ዓ.ም የደርግ መንግስት ከራሻ መንግስት በተደረገ ስምምነት ሆኖ “ከእኛ ትራክተር ውጪ ሌላ ማምረት ኣትችሉም” በሚል ቅደመ ሁኔታ ነበር። በዚህ ሂደት ላይ እስከ 2003 ዓ.ም ኣንድ ዓይነት ትራክተር/ተመሳሳይ የፈረስ ጉልበት ያለው/፣ በድምሩ ከ500 የማይበልጡ፣ SKD (Semi Knock Dawn) ሆነው የመጡትን ትራክተሮች ከመገጣጠም ኣልፎ በCKD (Complete Knock Dawn) ደረጃ ተበትነው የመጡትን ትራክተሮች ይገጣጥም እንዳልነበረ፣ የራሱ ትራክተር የማምረት ሂደትም በ30 ዓመታት ውስጥ ከ30% ይበልጥ እንዳልነበረ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰጡት ቃል ማረጋገጥ ይቻላል።

በተመሳሳይ በፈጣን እድገት የራሳቸው ቴክኖሎጂ በማልማት በዓለም ላይ ጥሩ ምሳሌ ናቸው የሚባሉ የኤሽያ ኣገሮች ቴክኖሎጂውን ከምዕራቡ ዓለም እንዴት እንደቀዱት፣ እንዴት እንዳለሙት እና እንዳስፋፉት ማንም ሰው የሚረዳው ነው። ይህ ዓለማዊ እውነታ ዓቃቤ ህግ ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ከዓመት ዓመት በመደበኛነት እንደሚጠቀሙበት ወረቀት፣ ቀለም፣ ሶፍት… ዓይነት እቃ በጨረታ መገዛት ነበረበት በሚል ያቀረበው ክስ በኣንድ በኩል የመንግስት ኣቅጣጫና ስትራተጂን ያላገናዘበ በሌላ በኩል ሊሆን የማይችል ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ኣገሪቷ ሙሉ ትራክተር ለመግዛት የሚያስችል ገንዘብ ሲኖራት እና ቴክኖሎጂ የማልማት ስትራተጂ ሳይኖራት ሲቀር ነው።

መንግስት ከላይ የተገለፀውን ስትራተጂ የነበረው እና ሜቴክ እንዲያስፈፅመው ተልእኮ የተሰጠው ስለመሆኑ በክስ ቻርጁ እና በሂደቱ ላይ በዓቃቤ ህግ በኩል ለመደበቅ የተሞከረ ቢሆንም ኣቶ ሃብታሙ መኮነን የተባሉ 5ኛ የዓቃቤ ህግ ምስክር ለህዝብ በተሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልሚም ሆነ በችሎት ቀርበው “…ትራክተሮቹ በመንግስት ኣቅጣጫ ነው ተገዝተው የመጡት…” በማለት በድፍረት ተናግሯል።ትራክተሮቹ በብዛት ማምረት የተፈለገበት ዓላማም በወቅቱ በመንግስት ተይዘው ለነበሩ የግብርና ኢንዳስትሪያላይዜሽን፣ የገጠር ኣክሰስ ፕሮግራም/URAP/፣ የስኳር ኣገዳ እርሻዎች እና ሌሎች ሰፋፊ እርሻዎች መሆኑን ምስክሮች እና ሰነዶች ያስረዳሉ።

ሜቴክ በግዢ መመሪያው ኣንቀፅ 21 ላይ “ከአንድ ወይም ከጥቂት አምራቾች ጋር በመደራደርና የረጅም ጊዜ ኮንትራት በመፈራረም የቴክኖሎጂ ችግርን ለመቋቋም ወይም የአቅርቦት አስተማማኝነትን ለማራጋገጥ ሲባል ከሌሎች አማራጭ የግዥ ስልቶች ይልቅ በኮንትራት ግዥ ዘለቄታ ያለዉ ጥቅም የሚገኝበት መሆኑን ከተረጋገጠ በኮንትራክት ግዢ ኣማካኝነት ግዢ መፈፀም እንደሚቻል ይደነግጋል። ይህ የግዢ ዘዴ በየትኛውም የሃገሪቱ ህጎችና መመሪያዎች ተደንግጎ ኣይገኝም። በሜቴክ የግዢ መመሪያ በልዩ ሁኔታ የተካተተበት ምክንያት ተቃሙ ከሚሰራው ስራ ኣንፃር ተገቢ በመሆኑ ነው። በዚህ መሰረት የኣዳማ እርሻ መሳሪያዎች እና ኢትዮ ፓወር የተባሉ የሜቴክ ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን የቴክኖሎጂ ችግር ለመቋቋም እንደ ቅደም ተከተላቸው የትራክተር እና የፓወር ፕላንት ተርባይን ውል ኣጋር ከሆኑ ኣምራች ድርጅቶች መፈራረማቸው ትክክለኛ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ ሳለ ይህ ተጣምሞ ክስ ሆኖ ቀርቧል።

2.1.7 ዓቃቤ ህግ ግዢው ‘እቅድና በጀት የነበረው ኣይደለም’ በማለት በበርካታ ክሶች የገለፀ ቢሆንም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመዝገብ ቁጥር 229443 (የመርከብ ጉዳይ) ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ላይ ሜቴክ የመንግስት የልማት ድርጅት እንደሆነና የሚተዳደረውም በመንግስት በሚመደብለት በጀት ሣይሆን በራሱ ገቢ በመሆኑ ልክ እንደ መንግስት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ አስተዳደሩ በዓመታዊ እቅድና በጀት የተወሠነ እንዳልሆነ በማረጋገጥ ምላሹን ሰጥተዋል። በአዋጅ ቁጥር 25/84 አንቀጽ 3(2)(ሀ) ላይ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚነት የላቸውም ተብለው ከተሻሩ ህጎች ውስጥ አንዱ የመንግስት ገንዘብ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያና ማስተባበሪያ አዋጅ ቁጥር 163/1979 እንደሆነ ተመልክተዋል።

ከዚህም በኋላ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር ህግ አልወጣም። በዚሁ አዋጅ ከአንቀጽ 23 እስከ 34 ድረስ ስለ ድርጅቶች ሂሣብ አመዘጋገብና ኦዲት በሚደነግገው ክፍል ላይ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች በተለየ የሂሣብ መዝገብ እንደሚዘጉና ሂሣባቸውም በጠቅላይ ኦዲተር ሣይሆን ተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑ በሚመድበው የውጪ ኦዲተር አማካኝነት የኦዲት ሥራ የሚሠራ መሆኑ ሲታይ ዓ/ህግ የህግ መሰረት የሌለው ክስ ማቅረቡን ያረጋግጣል። የፌዴራል መንግስት የግዢ ኣፈፃፀም መመሪያ ለሜቴክ ተፈፃሚነት ኣለው በማለት ዓቃቤ ህግ ያስቀመጠው የህግ መሰረት የለውም። መመሪያ በትርጉም ክፍሉ ላይ በበጀት በሚተዳደሩ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ብቻ ተፈፃሚነት እንዳለው ያስቀምጣል። በተመሳሳይ የፌዴራል መንግስት የግዢና ንብረት ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር 649/2001 በትርጉም ክፍሉ ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ በበጀት በሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ብቻ ተፈፃሚነት እንዳለው የደነገገ በመሆኑ የዓቃቤ ህግ ክስ ከመመሪያው እና ከኣዋጁ ኣንፃር ያቀረበው የህግ መሰረት የሌለው ሆኖ ሳለ በዚህ ተዛብቶ በቀረበው ክስ በርካታ ሰዎች ኣለ ኣግባብ ታስረው ይገኛሉ።

2.1.8 የመርከቦቹ ሽያጭ በዓለም ኣቀፍ ጨረታ መሆን ነበረበት በሚል ዓቃቤ ህግ የጠቀሰው ቢሆንም ይህ ነጥብ በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ መዝገብ ካቀረበው ክስ እና ከሰነዶቹ ጋር እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ምክንያቱም ዓቃቤ ህግ በየቀኑ ለያንዳንዱ መርከብ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ የሚወጣ መሆኑን በማመን መርከቦቹ ተሎ ወደ ሽያጭ፣ ወደ ማስወገድ ወይም ወደ ስራ መሰማራት ያለባቸው መሆኑን ያስቀምጣል። በሌላ በኩል በግልፅ ጨረታ መደረግ የነበረበት መሆኑን ጠቅሶ ክስ ያቀርባል። በጨረታ ይሸጥ ከተባለ ጨረታ ለማውጣት፣ የጨረታ ሰነድ ለመገምገም… ወዘተ የሚወስደውን ጊዜ እና በእነዚህ ጊዜ የሚወጣውን ወጪ ሲታይ ተጨማሪ ኣላስፈላጊ ወጪ የሚያወጣ በመሆኑ ዋና ዳይረክተሩ በመረዳታቸው በኣጭር ጊዜ ከእጃችን የሚወጣበትን ኣማራጭ ተከትላችሁ ሽጡ ብለው ኣመራር መስጠታቸው ተገቢ ነው። የመርከብ ዓቢይ ኮሚቴም የመርከብ ስራው እና የብረት ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት በወቅታዊ የገበያ ዋጋ እንዲሸጡ የውሳኔ ሓሳብ ኣቅርቦ በ28 ቀን ማለትም እስከ 30/02/2009 ጨርሱ በማለት መመሪያ መስጠታቸው ይወጣ የነበረውን ወጪ ለማዳን መሆኑ ግልፅ ነው።

የመርከብ ኣሻሻጭ ሂደትም በኣለም ኣቀፍ ደረጃ በኮሚሽን እጄንት/በደላላ/ ኣማካኝነት ተወዳዳሪዎች እንዲቀርቡ ተደርጎ መሸጥ የተለመደ ኣሰራር መሆኑን ኢባትሎድ በ19/11/2004 ዓ.ም የፃፈው ሰነድ ያረጋግጣል። ሽያጭ በሚያወጣህ መሰረት የምታከናውነው እንጂ እንደ ግዢ የራሱ መመሪያ ያለው ስለመሆኑ ዓቃቤ ህግ ጠቅሶ ያቀረበው ህግም ሆነ መመሪያ የለም። መንግስት መርከቦቹ እንደጠፉ ወይም የት እንደሌሉ እንደማታወቅ ዶክመንተሪ ፊልም በመስራት የተከሳሾቹ እና የቤተሰቦቻችንን ማሕበራዊ ህይወት ሆን ተብሎ እንዲናጋ የተደረገ ቢሆንም መርከቦቹ ግን በህጋዊ መንገድ ኮሚቴ ተወቅሮ የተሸጡ እና የሽያጭ ገንዘባቸው ለሜቴክ ገቢ የተደረገ መሆኑን ዓቃቤ ህግ በመዝገብ ቁጥር 229443 ያቀረበው 3ኛ ክስ በራሱ ያረጋግጣል።

2.1.9 ዓቃቤ ህግ በመዝገብ ቁጥር 229722 (የትምህርት ጉዳይ) በ2ኛው ክስ ላይ “…በምን ኣግባብ እንደተወሰነ ሳይታወቅ…ክፍያው ለመፈፀም ምንም ዓይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር…” ዋና ዳይሬክተሩ ለተማሪ ማርዳ መለስ የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲፈፀም ኣዝዟል የሚል ነው። ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ማሕበራዊ ግዴታ (Social Responsibility) ያለባቸው እና ኃላፊነታቸው መወጣት የሚኖርባቸው ስለመሆኑ ድሮም ሆነ ኣሁን በየተከሰተው ችግር መዋጮ ሲያዋጡ፣ ስፖንሰር ሲያደርጉ በእለት ተእለት ህይወታችን የምናየው የተለመደ ክስተት ነው። መንግስት ለህዝብ ባሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም ከ26ኛው ደቂቃ 47ኛው ሴኮንድ ጀምሮ በተላለፈው ላይ ‘ሜቴክ ከ100 ሚልዮን ብር በላይ ለተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት ስፖንሰር ማድረጉን፣ ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ደግሞ ድጋፍና ብድር መስጠቱን’ ይናገራል። ክፍያ በተለይ ደግሞ ስፖንሰርሽፕ በምን ኣግባብ መቅረብ እንዳለበት፣ እንዴት መወሰን እንዳለበት እና ማን መወሰን እንዳለበት ዓቃቤ ህግ የጠቀሰውም ሆነ ያቀረበው ማስረጃ የለም።

በክሱ ላይ “በምን ኣግባብ እንደተወሰነ ሳይታወቅ” የተባለ ቢሆንም የቀረቡት የዓቃቤ ህግ ሰነዶች ቀደም ብሎ ቃል መገባቱን፣ የገባው ቃል ደግሞ ተማሪ ማርዳ መለስ የትምህርት ክፍያ መፈፀም መሆኑን፣ (ይህች ግለሰብ ምንም እንኳ በክሱም ሆነ በሰነዶቹ የኣያት ስሟ ያልተጠቀሰ ቢሆንም የቀድሞ የኣገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስቴር ልጅ የሆነችው ማርዳ መለስ ዜናዊ መሆኗ ይታወቃል) የሚከፈለውም የመጀመሪያው ክፍያ ኣሜሪካ ለሚገኘው ሲራከስ ዩኒቨርስቲ መሆኑን፣ ኮርፖሬሽኑ ይህንን ያደረገው ለኣገር ሲለፋ የሞቱትን የኣገሪቱ መሪ በመሞታቸው ምክንያት ልጃቸው ትምህርቷ በኣግባቡ እንድትከተታል ኃላፊነቱ ሜቴክ እንዲወጣ ተቋሙ ቃል የገባ መሆኑን ሰነዶቹ ያሳያሉ። የቃል መግባት ጉዳይ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ኣስገዳጅ ህግ በሌለበት እና ባልተገለፀበት እንዲሁም ዋና ዳይሬክተሩ ተቋሙን ወክሎ ያደረገው እና የፃፈው ደብዳቤ መሆኑ እየገለፀ በምን ኣግባብ እንደተወሰነ ሳይታወቅ ተብሎ የቀረበው ክስ የዘመቻው ኣንድ ኣካል ኣድርጎ ስም ለማጥፋት እንጂ በመመሪያ ኣንቀፅ 25.1 መሰረት ከፍተኛ ግዢ በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ መከናወን እንደሚችል እየደነገገ የስፖንሰር ክፍያ ለመወሰን ስልጣን ኣልተሰጠውም ሊባል ኣይችልም።

ሜቴክ ስፖንሰር ካደረጋቸው ብሮች ተመርጦ ይሄ ጉዳይ ብቻ በክስ መልኩ የቀረበበት ዓላማም ማንም የሚረዳው ነው። ክፍያው ለመፈፀም ‘ህጋዊ ምክንያት የለም’ የተባለ ቢሆን ጉዳዩ ወንጀል እንደመሆኑ መጠን ይህ ክፍያ ‘ህገወጥ የሆነበትን ምክንያት እና የተጣሰ ኣሰራር ስለመኖሩ’ ዓቃቤ ህግ የጠቀሰው ወይም ኦዲት ኣስደርጎ ያቀረበው ሰነድ የለም። በኣንፃሩ በክፍያ ሰነዶቹ በዋና ዳይሬክተሩ ከታዘዘ በኋላ በተዋረድ የሚገኙ ኃላፊዎች እንደየ ኃላፊነታቸው ሰነዱን ሲመሩት የነበረ መሆኑን፣ የውጭ ምንዛሪው ክፍያ እንዲከፈል በጣምራ ፊርማ ሲያዙ የነበረ መሆኑን፣ በባንክ ወጪ ማመሳከሪያ ሰነዱም ኣዘጋጅ፣ ኣረጋጋጭ እና ኣፅዳቂ ተብለው የሚመለከታቸው ኃላፊዎች እውቅና ሲሰጡት የነበረ ስለመሆኑ ሰነዱ ያስረዳል። በዚህ የፋይናንስ ሂደት እና በፋይናንስ ህግ መሰረት ‘የግድ ኣስፈላጊ የሆነ እና መቅረብ ይገባው የነበረ ነገር ግን ያልቀረበ ሰነድ’ ስለመኖሩ ተገልፆ የቀረበ ማስረጃ የለም።

ይህ ክፍያ ህገ ወጥ የሆነበት፣ ህገወጥ ሊያስብለው የቻለውን የኣሰራር ጥሰት ወይም የትኛው ህጋዊ ምክንያት? የትኛው ህጋዊ ያልሆነ ምክንያት እንደሆነ የሚደነግግ መመሪያ ወይም ኣሰራር ስለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ሳይገልፅ እና ማስረጃ ሳያቀርብ በድፍኑ የቀረበው ክስ ለፖሎቲካው ፍጆታ ነው። በክሱ ላይ ለተማሪ ማርዳ መለስ የተከፈለው ገንዘብ 1.2 ሚልዮን ብር ገደማ ነው። ለኣገሪቱ የቀድሞ መሪ ልጅ ይህ ገንዘብ ስፓንሰር ማድረግ ተገቢ ነው ወይስ ኣይደለም? በጓሮ በር የሚደረገው ተደርጎ ቢከፈል ይሻል ነበር ወይስ በግልፅ ደብዳቤ ኃላፊነት በመውሰድ የሚለውን ማንም ሰው የሕሊና ፍርድ ሊሰጥበት ይችላል።

2.1.10 ከትራክተር ውል መፈራረም እና ማፅደቅ በተቋሙ መመሪያዎች ለተከሳሾቹ የተሰጠ ስልጣን ሆኖ ሳለ ኣስቀድመው ከሻጮች ጋር ተገናኝተው ወስነውት ነው እየተባለ የቀረበው ፍሬ ነገር በማስረጃ የማይረጋገጥ፣ ሊረጋገጥም የማይችል እና እስከ ኣሁንም ምንም ዓይነት ምስክር ያልቀረበበት ተከሳሾቹ ያከናወኑት ስራ ለማጠልሸት የተገለፀ ነው። ለምሳሌ URSUSS ከተባለ የፖላንድ መንግስት ኩባንያ የተፈረመውን ውል ስናየው የፖላንድ ፕሬዚዴንትን ጨምሮ የሁለቱ ኣገሮች ኣመራሮች ስራውን በመጎብኘት ድጋፍ እና ክትትል የሚያደርጉለት መሆኑን የዓቃቤ ህግ ምስክሮች መስክሯል። ውል ሊታሰር የቻለው ዓቃቤ ህግ በክሱ እንደገለፀው እና በማስረጃም ያላረጋገጠው ‘በሬ ወለደ’ ዓይነት ፈጠራ ሳይሆን በወቅቱ ሁለቱም ኣገሮች ጀርመን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ (በኣምባሳደሩ እና የኤምባሲው Commercial Attaché) ኣማካኝነት የፖላንድ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የ100 ሚልዮን ዶላር ኢንቨስትመት ለማድረግ ተስማምቶ ከዚህ ውስጥ 90 ሚልዮኑ የሚሆን በጋራ ማምረት/መስራት/ እቅድ ውስጥ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ከፖላንድ ኩባንያዎች ጥሬ እቃ ሊገዛቡት ሌላው በድጋፍ መልኩ ሊሰጥ ስምምነት የተደረሰበት ነው።

ይህ ስምምነት ከሁለቱም መንግስታት ጋር ስምምነት እስኪደረስ ሜቴክ ጀርመን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኣማካኝነት ከኡረሰስ ጋር ድርድር በማድረግ የተለያዩ ውሎች ያደረገ ቢሆንም የመንግስት ለመንግስት ድርድሩ ኣልቆ የብድርና የእርዳታ ስምምነቱ/Tied Aid Credit/ እ.ኤ.ኣ የካቲት 25 ቀን 2014 (የካቲት 18 ቀን 2006 ዓ.ም) ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ በኣቶ ኣሕመድ ሽዴ እና በፖላንድ መንግስት ተፈርሟል። ይህ ስምምነትም በኣዋጅ ቁጥር 831/2006 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ውሉ የተፈረመው መንግስት ከመንግስት ሆኖ ከፖላንድ በኩል የፈረመው በኢትዮጵያ የሚገኘው ኣምባሰደሩ በመሆኑ ከሜቴክ በኩል ደግሞ ተመጣጣኝ ኃላፊነት ያለ ሰው መፈረም ስለ ኣለበት በዋና ዳይሬክተሩ በኩል ተፈርሟል። ይህም በግዢ መመሪያው ኣንቀፅ 40 መሰረት የውጭ ብድር ያለበትን ግዢ በማለት በግልፅ የተፈቀደ ሆኖ ሳለ እውነቱ ተደብቆ በክስ መልክ ቀርቧል።

2.1.11 ዓቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የተሰራው የሞባይል ማስፋፋያን በተመለከተ ስራው ይመራው የነበረው ኣስተባባሪ ኮሜቴ (Steering Committee) የተቋቋመበት መንገድ ህገ ወጥ እንደሆነ፣ ህጋዊ እውቅና የሌለው ወይም Formally ያልተቋቋመ እያለ በክሱ የሚገልፀው ቢሆንም በመጋቢት 2008 በፀደቀው ‘Inception Plan for the organization of NGN program/Project Coordination and Supervision Office NGN – (PCSO) for Vendor Financing Projects’ በሚለው ሰነድ (ገፅ 152) ላይ በዋና ስራ ኣስፈፃሚ የሚመራ ኣስተባባሪ ኮሚቴ እንደሚዋቀር ይገልፃል። ጠቅላላ የፕሮጀክቱ ኣመራር በሚያሳየው Organogram ቻርትም (ገፅ 154 ላይ) ኮሜቴው ስራውን በበላይነት የሚመራ መሆኑን ያስረዳል። የኮሜቴው ፀሓፊ የነበረው ‘ኣቶ ዘላኣለም በቀለ’ የተባለው ግለሰብ በኦዲት ክፍሉ ለቀረበለት የፅሑፍ ቃለ መጠየቅ ሲመልስ ኮሚቴው የፖሊሲ ግብኣቶችን እንዲሰጥ እና በበላይነት እንዲያስተባብር በቦርድ በፀደቀ መመሪያ እ.ኤ.ኣ በ2008 በቦርድ መዋቀሩን፣ ለተከታታይ 3 ዓመታት በየእለቱ ዓርብ እየተገናኘ 136 ጊዜ ስብሰባ ያደረገ መሆኑን፣ ሰብሳቢው የቀድሞ ስራ ኣስፈፃሚ ኣቶ ኣማረ ኣምሳሉ ሆነው በኣባልነት ደግሞ የቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል እና ሌሎች ኣባላት እንደሚገኙበት ይገልፃል።

ዓቃቤ ህግ የኮሚቴው ስራ እና ኃላፊነቱ የሚገልፅ ሰነድ የለም ይበል እንጂ ምን ምን እንደሚሰራ በእነዚህ ሰነዶች ተቀምጧል። ኣደረጃጀቱ እና የኣባላቱ ኣመራረጥን በተመለከተ ‘ሰነድ ነበር’ ከቦርድ ፅ/ቤት ጠይቁ በማለት የኮሚቴው ፀሓፊ ገልጧል። በኢትዮ ቴሌኮም ህግ ክፍል ኃላፊ ግንቦት 05 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ላይ “…የኮሚቴው ኣመሰራረት፣ ስብጥር እና ኃላፊነት የሚያሳይ ሰነድ በፕሮጀክት ክፍሉ (NGPO) የሌለ መሆኑን የሚመለከተው የስራ ክፍል (የቴክኒክ ዋና ክፍል) ያረጋገጠ መሆኑን በኣክብሮት እንገልፃለን” ብሏል።

ነገር ግን ደብዳቤው ላይ የሰፈረው በሁለት መንገድ ስህተት ነው። በኣንድ በኩል NGPO/የስራ ክፍሉ የተባለው/ ኣሁን የለም/ፕሮጀክቱ ሲያልቅ ተዘግቷል/። ስለዚህ ሰነድ ሊሰጥ ኣይችልም። በሌላ በኩል በዚህ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው የዛሬ 7 ዓመት ገደማ በኦዲቶሮቹ ሲጠየቅ “በእኛ በኩል የለንም፣ ከሚመለከተው ጠይቁ” ብሎ ምላሽ ሰጥቶዋችዋል። ኮሚቴውን ያቋቋመው ቦርዱ መሆኑን፤ ማቋቋሚያ ሰነዱም የፀደቀው በቦርዱ መሆኑን፣ ስብጥሩን የሚሳይ ሰነድም ‘በቦርዱ ኣለ’ ከቦርዱ ወይም ኮሚቴው በሰብሳቢነት ከሚመራው ዋና ስራ ኣስፈፃሚ ጠይቁ እየተባለ እና እየተገባ ሌላ የስራ ክፍል መጠየቅ ያውም ‘በNGPO ይገኛል ሳይባል’ ፍትህ ለማዛባት ተፈልጎ ማረጋገጫ ደብዳቤ ከማይመለከተው ክፍል እንዲቀርብ ተደርጓል።

(ይቀጥላል) 
See Les

የጭቁኖች ድምፅ (Source: Facebook)

 



 

Yemen: Houthis Kill, Expel Ethiopian Migrants

Reply Note to the Appeal Letter

 

 

Thursday, August 13, 2020

ATV: መልእክት ለ ዶር አብይ - Message to Abiy Ahmed

 

Bring back Ethiopian migrants to their home! (Source: Humans of Tigray)

 

ብሓውና ሃፍቱሽ ዝተለቀቀጥ ድምፂ ውፁዓት እሱራት ኣሕዋትና ትገልፅ እያ ንሕና እውን ኣብዛ ሊንክ እናኣተውና ነተባብዓዮ ሼር ክዓ ንሓግዞ በርትዕ #ሃፍቱሽ። (Source: https://youtu.be/EHWGLGNRFE0)

 

 

ወፍሪ ሓርነት - Wefri Harnet

 ከሜቴክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኣገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ተይዘው የተከሰሱ ግለሰቦችን ጉዳይ ኣስመልክቶ የተሰራ ማጠቃለያ።

ይህ ማጠቃለያ ከኣያያዛቸው፣ ክስ ኣመሰራረቱ እና እስክ ኣሁን በፍርድ ሂደቱ የሆነውን ነገር ከህግ፣ ከሞራል፣ ከፍትሓዊነት እና ከጤና ኣኳያ የሚያትት ነው።

(ክፍል 1)

ሀ/ ኣያያዛቸውን በተመለከተ

1. መንግስት በፍትህ ተቋማት ይሰሩ በነበሩ ሰራተኞች ያቀረበው ክስ ያለ ፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ ይይዙ ነበር የሚል ነው። ነገር ግን ከሜቴክ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከማረሚያ ቤት የተያዙ ግለሰቦች ኣንዳቸውም በመያዣ ትእዛዝ ኣልተያዙም። በኣንፃሩ ‘ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ’ ተብለው በየተቋሞቻቸው ከተጠሩ በኋላ ስብሰባው ፌዴራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ ነው ተብለው ሲሄዱ ‘ለምርመራ እንደሚፈለጉ’ ተነግሯቸው የታሰሩ ናቸው።

2. የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከሌላ ኣንድ ጀነራል ጓደኛቸው ጋር ቀድሞ የተዘጋጀ ስልጠና ለመስጠት ወደ ዳንሻ በሚሄዱበት ወቅት በትግራይ ክልል ፖሊስ ኣማካኝነት እንዲቆሙ ተደርገው ‘መኪናችሁ የጦር መሳሪያ ይዛለች ተብሎ ተነግሮናል’ ብለው ከፈተሹ በኃላ የመከላከያ ኣባላት መጥተው እንዲሰጥዋቸው የትግራይ ፖሊስ ኣባላትን ሲጠየቁዋቸው ‘እናንተ ይህንን ለማድረግ ስልጣን የላችሁም፣ የመያዣ ትእዛዝ ያለው ካለ መያዣ ትእዛዙን ይዞ ይምጣ’ ከተባሉ በኋላ የፌዴራል ፖሊስ ኣባላት በሄሊኮፕተር የመያዣ ትእዛዝ ይዘው በመምጣት ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል። በመያዣ ትእዛዙ ስማቸው ያልነበረው ሌላኛው ጓደኛቸው ግን ወደ ስራቸው ኣምርተዋል። በመኪናው ሁለቱ ጀነራሎች ከያዙት ሽጉጥ፣ የስልጠና ሰነዶች እና 2000 ብር ውጭ የተገኘ ነገር ኣልነበረም። ጀነራሉ የተያዙበት ቦታ ከሱዳን ድንበር 70 ኪሎ ሜትር የሚርቅ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት እና መንግስት ባሰራጨው ዜና ላይ ከኣገር ሊሸሹ ሲሉ ተያዙ በሚል ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ስራ ተካሂዶባችዋል። በተመሳሳይ የቀድሞ የደህንነት ተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኣቶ ያሬድ ዘሪሁን በዱከም ከተማ ውስጥ በማረፊያቸው የተያዙ ሆነው ሳለ ወደ ኬንያ ለመሄድ በድንበር ተያዙ የሚል ሓሰተኛ ዜና መንግስት ኣሰራጭቶባችዋል።

ለ/ የቀረበባቸውን ክስና ማስረጃን በተመለከተ

1. በጊዜ ቀጠሮ ወቅት

በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ምርመራው ሲያደርግ የነበረው ፖሊስ ሳይሆን ዓቃቤ ህግ ነበር። ይህንን ጉዳይ የሚመሩ እና የሚመረምሩ ዓቃቤ ህጎች እና ፖሊሶች ኣንድም የትግራይ ተወላጅ ወይም ለነበረው ስርዓት ጥሩ ኣመለካከት ያለው ሞያተኛ እንዳይኖራቸው ተብሎ በተሰጠ ኣቅጣጫ መሰረት በወቅቱ የተደመሩ ወይም የድሮ ስርዓት ተጠቂ ናቸው የተባሉ ሞያተኞች የተደራጁበት ነበር። ይህ ኣካሄድ ትክክል ኣይደለም ያሉ በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ይሰሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ይህንን በማለታቸው በደረሰባቸው ጫና ከስራቸው እንዲለቁ ተገደዋል። እንደዛም ሆኖ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ክርክር ከህግ ኣንፃር ሲታይ፡-

1.1 ምርመራ የተጠርጣሪውን ማሳር የግድ ኣስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተጠርጣሪው ከማያዝክ በፊት ማስረጃዎች ተሰብስበው፣ ተጠርጣሪው ወንጀል መፈፀሙን የሚያሳዩ መነሻዎች በኣግባቡ ተይዘው ከፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ በመጠየቅ ሰው የሚያዝበት ሂደት ነው። የኣሁኑ መንግስት ወደ ስልጣን በመጣ በማግስቱ እውቅና የሰጠው እና እተገብረዋለሁ ያለውን ለኢትዮጵያ ህዝብ “…ከዚህ በኋላ ኣጣርተን እንጂ ኣስረን ኣናጣራም…” በማለት ነግሮ ነበር ። ኣባባሉ ትክክለኛ የህግ ኣካሄድ ነው። ነገር ግን በተግባር ኣልተፈፀመም። ምሳሌ 1 በመዝገብ ቁጥር 238040 እነ ጌታቸው ኣሰፋ የተከሰሱት 6ኛ ተከሳሽ ኣቶ ተስፋዬ ኡርጌ እና 26ኛ ተከሳሽ ኣቶ ማርክስ ፀሓዬ ከጉዳዩ ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር ሳይኖር ቦንቡ ከፈነዳበት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዋዜማ ላይ የተከሰተውን ‘በተቋሙ የተለመደ ኣሰራር’ ከቦንቡ ፍንዳታ ጋር በማያያዝ ስማቸው እንዲጠፋበት ተደርጓል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በስልጣን ያለ ኣግባብ መገልገል በሚል በሌላ ጉዳይ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ ኣልተመሰረተባቸውም። ምሳሌ 2 ሁሉም ከሜቴክ፣ ከደህንነት ተቋሙ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከማረሚያ ቤት እና ከቴሌ የተያዙ ሰዎች ለምርመራ በሚል በኣማካኝ ከ4 ወር በላይ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባችዋል።

1.2 ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዳይወጡ በሚል ኣንድ ዓይነት እና በኣንድ ጊዜ የቀረበ ጥቆማን ‘ለጊዜው ብቻ’ በተለያየ መዝገብ በማደራጀት ጉዳዮችን ሰነጣጥቆ በማቅረብ፣ በኣንዱ ዋስትና ሲፈቀድ ‘ሌላ ኣዲስ ጥቆማ መጥቷል’ እየተባለ ዋስትና የማስከልከል ስራ ተሰርቷል። ለምሳሌ በመዝገብ ቁጥር 225258 እና 232121 ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች 6 ጊዜ ዋስትና ፈቅደውላቸው ፖሊስ እና ዓቃቤ ህግ ተጠርጣሪው ኣዲስ ጥቆማ ቀረበባቸው እያሉ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስ ሲመረምረው የነበረውን የቴሌ ታወር (በመዝገብ ቁጥር 240375 በኋላ ላይ ክስ የሆነውን) ጉዳይ ጭምር በማቅረብ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን ዋስትና ለማስከልከል ኣላማ ሲጠቀምበት ነበር።

1.3 በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ተጠርጣሪዎቹ የፈፀሙትን ተግባር በህዝብ ዘንድ ሚዛናዊ እሳቤ እንዳይያዝ ፖሊስ የፈጠራ ምክንያቶችን ሲያቀርብ ነበር። ምሳሌ 1 ከደህንነት ተቋሙ የቀረቡ ተጠርጣሪዎች ጊዜ ቀጠሮ በሚያየው ችሎት ላይ “ተጠርጣሪዎቹ ከሚሰሩበት ክፍል መርዝ የተከማቸበት መጋዘን ተገኝቷል” እየተባለ ሲቀርብ ነበር። በዚህ ጉዳይ ግን መርዝ የተደረገበት ተበዳይ ነበር ወይም ተቋሙ መርዝ ተጠቅሟል የሚል ክስ ኣልቀረበም። በተመሳሳይ ተጠርጣሪዎች ያላደረጉትን ተግባር ኣድርገውታል ተብሎ በጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ደብዳቤ ላይ ተፅፏል፤ የተደረገውን ኣጋንኖ ማቅረብ እና በዜና ማሰራጨት ከምርመራው በላይ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጥበት ይደረግ ነበር። ምሳሌ 2 ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው በሚቀርቡበት ችሎት ላይ በሶማሌ ክልል የተሰራውን የሞባይል ማስፋፊያ ግንባታ ስራን በተመለከተ ተጠርጣሪው ‘ስራው ወንድማቸው ለሚመራው ኮርፓሬሽን ጥቅም ሲሉ በውል ሰጥቷል’ ተብሎ ሲቀርብ ነበር። ነገር ግን በኃላ ላይ ጉዳዩ በመዝገብ ቁጥር 240375 ክስ ሆኖ ከእነ ሰነዱ ሲመጣ ውሉን የፈረሙት የወቅቱ የቴሌ ስራ ኣስፈፃሚ መሆናቸውን፣ ውሉ በሚፈረምበት ጊዜ (በ2001 ዓ.ም) ሜቴክ ያልተቋቋመ እና ከመከላከያ ሚኒስቴር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተደረገ መሆኑን፣ ወንድማቸው ሜጀር ጀነራል ክንፈም የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት በ2002 ዓ.ም መሆኑን ዓቃቤ ህግ በክሱ ገልፆታል። በሰነድም ተረጋግጧል።

2. በመደበኛ የክስ ሂደት ወቅት

2.1 ዓቃቤ ህግ በህግ ወንጀል ሊሆኑ የማይችሉ ተግባራትን የሃገሪቱ ህግና የተቋማቶቹ መመሪያዎችን በሚጥስ መልኩ የወንጀል ድርጊቶች እንደሆኑ ኣድርጎ ክስ ኣቅርቧል። በህግ መሰረት መቅረብ የሚገባው ክስም ህጎች እና ኣሰራሮች ተጣምመው ከህግ ውጭ ኣቅርቧል። ለምሳሌ፡-

2.1.1 በሃገሪቱ የግዢ ህጎች መሰረት [የፌዴራል መንግስት የግዢና ንብረት ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር 649/2001 ኣንቀፅ 3(2)(ለ)] ኣንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ከሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት በሚያደርጉት ግዢ ላይ በኣዋጁ የተቀመጡ የግዢ ዓላማዎች፣ ስርዓቶች እና ሂደቶች ተከትለው እንድሄዱ ኣያስገድዳቸውም። በኣዋጁ ኣንቀፅ 79 ላይ ደግሞ ኣዋጁን የሚቃወም ማናቸውም ደንብ፣ መመሪያ እና ልማዳዊ ኣሰራር ተፈፃሚነት እንደሌለው ያስቀምጧል። ፓርላማው በቀድሞ የግዢ ህግ (ኣዋጅ ቁጥር 430/97) ያልነበረን ተጨማሪ ልዩ ሁኔታ በተራ ፊደል “ለ” በ2001 ዓ.ም ሲደነግግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በእርሳቸው ሲዋዋሉ/ግዢ ሲፈፅሙ/ መደበኛ የግዢ ስርዓቶችን እና ሂደቶች ይከተሉ ቢባል ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን፣ ከኣንድ መስሪያ ቤት ተቀንሶ/በኣንድ መስሪያ ቤት የደረሰ ጉዳት/ ወደ ሌላ መስሪያ ቤት ሲከፈል/ሌላኛው የመንግስት መስሪያ ቤት ሲያተርፍ/ ዞሮ ዞሮ ገንዘቡ ከመንግስት ቀኝ ኪስ ወደ መንግስት ግራ ኪስ የሚሄድ መሆኑን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በየዘርፋቸው በህግ ሲቋቋሙ የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም የማስጠበቅ ተመሳሳይ ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረጉ ነው። የሃገሪቷ ህግ በዚህ መልኩ የሚደነግግ ሆኖ ሳለ በኣቶ ኢሳያስ ዳኘው የተጀመረን የሶማሌ ክልል የሞባይል ማስፋፊያ ግንባታ ቴሌ ከመከላከያ ጋር ውል በማሰሩ በመዝገብ ቁጥር 240375 እነ ኣማረ ኣምሳሉ በሚል 10 ተከሳሾችን ተከሰውበታል። በመዝገብ ቁጥር 229443 ላይም ሜቴክ ከኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርስትና ሎጂስቲክስ ኣገልግሎት ድርጅት የሁለት መርከቦች ግዢ በማከናወኑ መደበኛ የግዢ ስርዓትን ኣለተከተሉም በሚል በ14 ሰዎች ላይ ክስ ሆኖ ቀርቧል።

2.1.2 የፌዴራል መንግስት የግዢና ንብረት ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር 649/2001 ኣንቀፅ 3(2) (ሀ ላይ እንደተደነገገው የደህንነት እና የመከላከያ እቃዎችን በተመለከተ በተለየ መልኩ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት እንደሚከናወን ተቀምጧል። ነገር ግን ዓቃቤ ህግ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተለየ መልኩ እንዲከናወን ያልወሰነ ስለመሆኑ ከተቋሙ ማረጋገጫ ሳያቀርብ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን በመዝገብ ቁጥር 248994 ላይ ወታደራዊ ራዳርን የሚመለከት እንዲሁም በመዝገብ ቁጥር 229497 ላይ በታንክ ላይ የሚገጠም የመድፍ መከላከያ /ERA BOX/ን የሚመለከት ውል በጨረታ መሆን ነበረባቸው ብሎ ክስ ኣቅርቧል።

2.1.3 የሜቴክ ዋና ዳይሬክተሩ በተቋሙ የግዢ መመሪያው በኣንቀፅ 25.1 ላይ ‘…ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ይረዳል ወይም የተለየ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ሲታመን በኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ትዕዛዝ መሠረት ልዩ ግዥ በማዕከል ሊፈፀም ይችላል’ በማለት ተደንግጎ ይገኛል። በሌሎች የግዢ ህጎች እና መመሪያዎችም በተቋሙ የመጨረሻው ኃላፊ ትእዛዝ ግዢ ሊፈፀም እንደሚችል ይደንግጋሉ። ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ስልጣን ተሰጥቶዋቸው እያለ ዓቃቤ ህግ ግን ስልጣን ሳይኖራቸው ግዢ እንዲፈፀም ኣዘዙ በሚል ተደጋግሚ ክስ ኣቅርቧል። ዋና ዳይሬክተሩ ጊዚያዊ ኮሚቴ በማቋቋም ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት ኣቅጣጫ መሰረት ግዢ ፈፅሞ እያለ በግዢ መመሪያው ያለውን ሌሎች የግዢ ዘዴዎች እና ሂደታቸው ኣልተከተሉም በሚል በበርካታ የተቋሙ ሰራተኞች ክስ ቀርቦባችዋል። ለኣብነት ያህል በመዝገብ ቁጥር 229498 (የሆቴሎች ግዢ) ፣ በመዝገብ ቁጥር 231823 (የጥገና ጉዳይ) ፣ በመዝገብ ቁጥር 249410 (የመኪኖች ግዢ) እና በመዝገብ ቁጥር 229443 (የመርከብ ጉዳይ) በተከሳሾች ላይ ኣለ ኣግብብ ክስ ቀርቧል።

2.1.4 ዓቃቤ ህግ በሜቴክ እና የቴሌ ግዢዎች ላይ ‘ግዢው በቦርድ ሳይፀድቅ እንደተገዛ የገለፀ ቢሆንም ይህ ስልጣን ከየት የመነጨ እንደሆነ ኣይናገርም። ሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ ወይም የተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ወይም የሌላ አካል ነው ለማለት በግልፅ የተከሣሾችም ሆነ የቦርድ ሥልጣን ወሰን መታወቅ አለበት። በአዋጅ ቁጥር 25/84 ላይ በምዕራፍ 3 ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አቋምና አመራር የተደነገገ ሲሆን በዚህ ምዕራፍ ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥን ካልሆነ በግዥ መግዛትን በተመለከተ ለቦርድ የተሰጠ ሥልጣን የለም። ይልቁንም በአዋጁ ኣንቀፅ 9(2)(ለ) እና ኣንቀፅ 18 መሠረት ኩባንያዎቹ በስራ ኣስኪያጆቻቸው አማካኝነት መብት ያገኛሉ፤ ግዴታ ይቀበላሉ ሲል ተደንግጓል። ዓቃቤ ህግ ቦርድ በቃለ ጉባኤ ይዞ ስለመፍቀዱ ማስረጃ የለም በሚል በርካታ ክሶች ያቀረበ ቢሆንም መጀመሪያው የቦርዱ ስልጣን ስለመሆኑ ግን የሚጠቅሰው ህግም ሆነ የሚያቀርበው ማስረጃ የለም።

ለኣብነት ያህል በኢምፔርያል ሆቴል ጉዳይ ላይ (229498) የሜቴክ ቦርድ ኣውቆት የተገዛ መሆኑን በወቅቱ የቦርድ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበረው ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ የተባለ የዓቃቤ ህግ ምስክር ኣረጋግጧል። ምስክሩ በችሎት ቀርበው “የሪቬራ ሆቴል ግዢ በኣጀንዳነት ተይዞ ለቦርድ እንዲቀርብ በኣጀንዳ ነጥብነት ተይዞ እንዲቀርብላቸው ሲደረግ ‘ቀደም ብላችሁ የኢምፔርያል ሆቴል ስለገዛችሁ’ ይህንን በኣጀንዳነት ኣንይዝም ብለው የቦርድ ሊቀመንበሩ ኣልተቀበሉትም’’ በማለት መስክሯል። በዚህ ምስክርነት ላይ የኢምፔርያል ግዢ ቀደም ብሎ ሲከናወን ቦርዱ ያወቀው እንደነበር ተረጋግጧል። ነገር ግን ቦርዱን ይመሩ የነበሩ ሰዎች በዚህ ጉዳይም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች በወሰኑት ውሳኔ፣ በሰጡት ኣቅጣጫ ስለተደመሩ ወይም የለውጡ ኃይል ኣካል ስለሆኑ ማንም ኣልጠየቃቸውም።

በተመሳሳይ በኣቶ ኢሳያስ ዳኘው ተጀምሮ ሌሎች 3 ሰዎች የተካተቱበት የዩኒቨርስቲ ኔትዎርክ ግንባታ(EthERNet) እና የሶማሌ ክልል የሞቦይል ማስፋፊያ ውሎች በኢትዮ ቴሌኮም (በቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፓሬሽን) ቦርድ መፅደቅ ሲገባቸው እንዳልፀደቁ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ቢሆንም በመንግስት የልማት ድርጅቶች ኣዋጅ ቁጥር 25/84 ኣንቀፅ 14 መሰረት ‘የረዥም ጊዜ የውጭ ብድሮችን’ ካልሆነ በስተቀር ግዢን በተመለከተ ቦርዱ እንዲያፀድቅ ስልጣን ኣልተሰጠውም።

ግዢ ማከናወን እና ማፅደቅ የማኔጅመንቱ የእለት ተእለት ስራ ሆኖ ሳለ የቦርድ ስራ እንደሆነ ተደርጎ ክስ ቀርቧል። ሃገሪቱ ለቴሌኮም ማስፋፊያ ከZTE 1.5 ቢልዮን ዶላር ብድር የተፈራረመች እና ብድሩ በወቅቱ ሃገሪቱን ይመራ በነበረው ድርጅት እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳይቀር እውቅና ተሰጥቶት ቦርዱ ኣፅድቆታል። ምስክሮቹም ብድሩ ሳይፀድቅ ስራው ሊጀመር እንደማይችል ኣስረድቷል።

ኣስተባባሪ ኮሚቴው EthERNetን እንዲሰራ የወሰነው ከዚህ ገንዘብ ላይ ነው። በተቃራኒው ስለመሆኑ ዓቃቤ ህግ በክሱ ኣልገለፀም፤ ማስረጃም ኣላቀረበም። ኣቶ ኢሳያስ ዳኘው ከ2003 ዓ.ም በኃላ ይመሩት የነበረው Next Generation Project Office (NGPO) የተባለው የስራ ክፍል ከተፈቀደለት በጀት ውስጥ 1.47 ቢልዮን ዶላሩን ተጠቅሞ ፕሮጀክቶቹ ጨርሷል። ጠቅላላ ፕሮጀክቶቹም ኦዲት እንዲደረጉ ዓለም ኣቀፍ ጨረታ ወጥቶ Trac-Automation በተባለ የካናዳ ኩባንያ ኦዲት ተደርጎ ዋጋውም ሆነ ጥራቱ በኣለም ኣቀፍ ስታንዳርድ መሰረት መሆኑን ኣረጋግጦ ሪፖርት ቀርቦ በቦርዱ ፀድቋል።

ነገር ግን ዓቃቤ ህግ በፕሮጀክቱ ላይ የተሰራው የክዋኔ ኦዲት ሳያቀርብ እና ጉዳዩም በትክክል ሳይረዳው ተከሳሽ በዋስትና እንዲወጣ በግዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ሲፈቀድለት ዋስትና ኣስከልክሎ በእስር ለማቆየት ብቻ ክስ እንዲሆን ኣድርጓል። በክርክር ወቅት ዓቃቤ ህግ ከኢትዮ ቴሌኮም የመጡ ምስክሮችን በማስጠናት ግዢው በቦርድ እንዲፀድቅ በ1997 የወጣው የቴሌ የግዢ መመሪያ በኣንቀፅ 1.1 ያስገድዳል በማለት እንዲመሰክሩ የነገራቸው ቢሆንም በዚህ ኣንቀፅ ላይ በቦርድ እንዲፀድቅ የሚያስገድደው የተቋሙ ቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና ዓመታዊ እቅድ (Annual Plan) እንጂ ግዢን ኣይደለም።

ነገር ግን የመመሪያው ግልፅ ድንጋጌ ዓቃቤ ህግ ኣጣምሞ በማቅረብ ፍትህን ለማዛባት ተጠቅሞበታል። በሶማሌ ክልል የተሰራው የቴሌ ታወር ግንባታም ሆነ ማስፋፊያው በተቋሙ ዓመታዊ እቅድ እና ቢዝነስ ፕላን የተካተተ ኣይደለም የሚል ማረጋገጫ ከቦርዱም ሆነ ከቴሌ የትኛውም ክፍል ኣልቀረበም። በኣንፃሩ በሶሜሌ ክልል የተገነባው የሞባይል ማስፋፊያ በሌሎቹ ክልሎች እንደተሰራው በመላ ሀገሪቱ እንዲሰራ ከታቀው የተካተተ ሆኖ በኣከባቢው ከኣልሸባብ እና ሌሎች ኃይሎች ውግያ የነበረ እና የፀጥታ ችግር በመኖሩ የቴሌ ስራ ኣስፈፃሚ ለጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሽሙ በፃፉት ደብዳቤ መሰረት መከላከያ እንዲሰራው የተደረገ መሆኑን ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።

(ይቀጥላል) 
See Less
124
19 Comments
108 Shares
Like
Comment
Share

Comments

Most Relevant


DW International News Report, August 12, 2020.